Jared Donis331 reviews58 followersFollowFollowOctober 3, 2022ተስፋዬ በ53 ዓመቱ ቢያልፍም ይህንን የመሰለ ድንቅ ማስታወሻውን ትቶልን አልፎአል። ልክ ነው፥ አወዛጋቢ ግለሰብ ነበር፤ ነገር ግን ድንቅ ደራሲነቱን መካድ አይቻልም። ይህን መጽሐፉን ምናልባት ለ3ኛ ግዜ ማንበቤ ነው። አራት መቶ ገጾቹን በጣት በሚቆጠሩ ቀናት ውስጥ ነው የጨርስኋቸው። በጽሑፍ የማንሰለቸውን ታሪክ መንገር ከሚችሉ ጥቂት ደራሲያን መካከል ተስፋዬ አንዱ ነው። እንኳን ይህንን ጻፈልን! በዚህ መጽሐፉ መጨረሻ ላይ ‘ከነገ ወዲያ ማናችንም ብንሆን በህይወት አንኖርም። በታሪክ በበጎ የመታወስ መብት ያለውም ከቶ የለም።’ ብሎ የመፈረጅ ነጻነትን ለአንባቢው ትቶታል፤ እውነቱን ነው። በተስፋዬ ላይ አለመስማማታችን ራሱ የሰውየውን ነጻ መንፈስ እና ውስብስብ ሰብዕናውን ይጠቁማል። በቀጣይ ቀሪዎቹን ሁለት ማስታወሻዎች የማነብብ ይሆናል።
Esayas Tamiru1 review3 followersFollowFollowReadJanuary 1, 2017not goodThis entire review has been hidden because of spoilers.