Jump to ratings and reviews
Rate this book

የደራሲው ማሰታወሻ

Rate this book

422 pages, Paperback

First published January 1, 2010

24 people are currently reading
605 people want to read

About the author

ተስፋዬ ገብረአብ

8 books94 followers

Ratings & Reviews

What do you think?
Rate this book

Friends & Following

Create a free account to discover what your friends think of this book!

Community Reviews

5 stars
22 (36%)
4 stars
15 (25%)
3 stars
8 (13%)
2 stars
10 (16%)
1 star
5 (8%)
Displaying 1 of 1 review
Profile Image for Jared Donis.
331 reviews58 followers
November 1, 2022
እነሆ የተስፋዬ ገብረአብ ሁለተኛው ማስታወሻ! እነዚህ ማስታወሻዎቹ ግዜ የፈረደላቸው (vindicated) ምስክርነቶች ይመስሉኛል። ዛሬ ሕወሓትን ከጥቅም ውጪ ያደረገውን የፖለቲካ ቁማር ተስፋዬ ቀድሞ በብዕሩ አብላልቶታል።

እውነት ነው፥ ያን ግዜ (ታትሞ አገር ውስጥ በድብቅ ይነበብ በነበረበት ሰሞን) ሳነብበው ጥላቻን እና መከፋፈልን የሚዘራ ጽሑፍ መስሎ ተሰምቶኝ አቋርጬው ነበር። አሁን ዞር ብዬ ሳየው ግን ተስፋዬ በማስታወሻው እውነቱን እየተናገረ ነበር። የከፋፋዩን ስርዓት ሸፍጥ በይፋ እና በዝርዝር በመተረኩ የእርሱን ጽሑፍ ከፋፋይና የጥላቻ አስመሰለበት እንጂ ሐቁን ነው ያቀረበልን። ለዚህ ሊደነቅ ይገባዋል።

የታፈኑ ብዙ ግፎች፣ ፍትሕ ያላገኙ ብዙ በደሎች እና ሰሚ አጥተው ማላገጫ የሆኑ ብሶቶች ደም፣ ላብ እና ዕንባ ሆነው ነው አገሪቱን እያመሱ ያሉት። መዘዙም የትግራይን ሕዝብ ጨምሮ ለብዙኃን ዕልቂትና ሰቆቃ ሆነ።

እውነቱን እየተናገርንና እየጻፍን የምንፈወስበትን ዘመን ያምጣልን። አለበለዚያ ግፍ እና በደል ሲታፈን አገር የማፍረስ አቅም አጠራቅሞ ይወጣል። ተረጋግተን እውነትን እየሰማን እንታረቅ እንጂ ሌሎች ሰዎችም ያለፈ የፖለቲካና ማህበራዊ ማስታወሻዎቻቸውን በግልጽነት ቢጽፉ ከዚህ የተለየ እውነት ሊነግሩን አይችሉም። ከነገሩንም ዋሽተውን ነው።

ተስፋዬ እንዲህ ብሎ ተንብዮ ነበር በዚህ ድርሳኑ (ገጽ 138)፤ እርሱን አስነብቤ ላብቃ፦

"በጥንት ዘመን የቡርቃ ወንዝ ውርደትን መሸከም ባለመቻሉ አካሉን ሰብስቦ ከመሬት ስር የመደበቁን ታሪክ ሰምተን ነበር። በዚህ በእኛ ዘመን አባይ እና ቡርቃ ውስጥ ውስጡን እየተገናኙ ወግ ሳይጀምሩ አልቀሩም። ወሬው እውነት ከሆነ ከሁለት አንዱ አይቀሬ ይሆናል። አባይ እንደ ቡርቃ አንገቱን ይደፋል። አሊያ ደግሞ አባይና ቡርቃ በአንድነት ተያይዘው በነፃነት መዘመር ይጀምራሉ. . . "

ተስፋዬ ድንቅ ማስታወሻ ትቶልን አልፎአል። ትናንትን አንርሳ!
Displaying 1 of 1 review

Can't find what you're looking for?

Get help and learn more about the design.