Jump to ratings and reviews
Rate this book

ኦሮማይ

Rate this book
በኤርትራ ክፍለሃገር ለረጅም ጊዜ የተካሄደውን ጦርነት ተንተርሶ ስለጦርነቱ ሂደት በጦር አዛዥነት በተሳተፉ ጀነራሎች እንዲሁም የሀገሩ መሪ በሆኑት ሰዎች ዙሪያ እንዴት ጦርነቱን እንደመሩትና እየመሩት እንደነበረ የሚያሳይ ታሪካዊ ልቦለድ ነው።

Paperback

First published January 1, 1975

233 people are currently reading
3607 people want to read

About the author

በዓሉ ግርማ

7 books494 followers
ደራሲ በዓሉ ግርማ በኢሊባቡር ክፍለ ሀገር ሱጴ በምትባል ሥፍራ በ1928 ዓ.ም. ተወለዱ። ዕድሜያቸው ለትምሕርት ሲደርስ የአንደኛ ደረጃ ትምሕርታቸውን በልዕልት ዘነበወርቅ ትምሕርት ቤት ፤ ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርታቸውን ደግሞ በጄኔራል ዊንጌት ትምሕርት ቤት አጠናቀዋል። ከዚያም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖሊቲካል ሳይንስ እና ኢንተርናሽናል ሪሌሽንስ የ ቢ.ኤ. ዲግሪ ያገኙ ሲሆን፤ በዚሁ ተመሳሳይ መስክ ከአውሮፓ የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።

ደራሲ በዓሉ ግርማ በተለይ በልብ ወለድ እና በፈጠራ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ከታወቁት የኢትዮጵያ የዘመኑ ደራሲዎች መካከል ተወዳጅነትና ዝናን ያተረፉ ዕውቅ ደራሲ ነበሩ። ከጻፏቸው በርካታ ድርሰቶቻቸው ውስጥ «ከአድማስ ባሻገር» የተሰኘው መጽሐፋቸው በሩስኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በቀድሞዋ የሶቪየት ሶሽያሊስት ሕብረት ሪፑብሊክ ቀርቧል። በተጨማሪም በጋዜጠኝነት ሙያም ስማቸውን ያስጠሩ፤ ሙያቸውንም ያስከበሩ ደራሲ ነበሩ። «የዛሬይቱ ኢትዮጵያ» ጋዜጣ፤ የመነን መጽሔት፤ የአዲስ ሪፖርተር መጽሔት፤ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በመሆን ከመሥራታቸውም ባሻገር፤ ብዙ ወጣት ጋዜጠኞችን ለማፍራት ጥረት አድርገዋል። አዲስ ሪፖርተር የተባለውን መጽሔትም ደረጃው ከፍ እንዲልና በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲገመገም አድርገዋል። በጋዜጠኝነት ሙያቸው በኢትዮጵያ ራዲዮ ሠርተዋል።

ደራሲ በዓሉ ግርማ ለኢትዮጵያ ሥነጽሑፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱና ብዙ ሥራዎችን ያቀረቡ ሲሆን፤ የመጨረሻው መጽሐፋቸው «ኦሮማይ» በመባል ይታወቃል። ይኼውም መጽሐፍ በወቅቱ በነበረው የደርግ መንግሥት ሊደገፍ ባለመቻሉ በ1976 ዓ.ም. ለደራሲው ሕይወት መጥፋት መንስኤ ሊሆን በቅቷል።

Ratings & Reviews

What do you think?
Rate this book

Friends & Following

Create a free account to discover what your friends think of this book!

Community Reviews

5 stars
287 (55%)
4 stars
104 (20%)
3 stars
41 (7%)
2 stars
33 (6%)
1 star
53 (10%)
Displaying 1 - 30 of 30 reviews
Profile Image for Tihut G..
4 reviews9 followers
July 22, 2015
I remember reading this book back in highschool and was mesmerized by it. I've read it more than once and the magic is still there. Hats off to the most amazing book written by በአሉ ግርማ
Profile Image for ntnl.
122 reviews19 followers
September 19, 2020
ሳንወለድ የነበረውን ያየነው፣ ከኛ ቀድሞ በነበረው ዘመን የኖርነው እንደ በአሉ እና በአሉ ያሉ ደራስያን ብእር ውስጥ ነው። የደራሲው ምርጡ ስራ ይሄ (ኦሮማይ) ይመስለኛል። በጋዜጤኛው ሕይወት ውስጥ የሚያልፉ ወይም አብረውት የሚኖሩ.. የሚነካቸው፣ የሚያያቸው፣ የሚሰማቸውን ሁሉ እንደ መንፈስ ወይም ጠባቂ አሊያም ታዛቢ መልአክ ሆነን ሁሉን እንድናይ፣ እንድንሰማ ኦሮማይ የምናብ ፈረስ ሆኖናል። ከሮማን እስከ ፊያሜታ.. ከአዲስ አበባ እስከ አስመራ አብረነው ተጉዘን.. አብረነው ደክመናል ለማለት የሚያሰኝ መጽሐፍ ነው።
በበአሉ ያየነውን የስነጽሑፍ ታማኝነት ማየት የምንችልባቸው.. የሚሰማንን የሚነግሩን.. ያያነውን የማይክዱን.. የበላንን የሚያኩልን ሌሎች ብዙ ደራሲዎች ቢኖሩን ብዬ ተመኘሁ።
This entire review has been hidden because of spoilers.
Profile Image for The Ethiopian girl.
14 reviews27 followers
May 7, 2019
I don't have any words to describe how amazing this book is, it made me feel like I was there with Tsegaye watching everything unfold. For me, Bealu Girma is undoubtedly the best author we ever had.
15 reviews
January 25, 2023
ከበዓሉ ግርማ ስድስት ረዣዥም ልብወለዶች ውስጥ ዝነኛው ኦሮማይ ነው፡፡

ኦሮማይ፤ በ1975 ዓ.ም. በማንኩሳ አሳታሚ ለህትመት ብርሃን በቃ፡፡ ርዕሱ ‹‹አለቀ፣ አበቃ፣ ደቀቀ›› የሚል ፍቺ የሚሰጥ የትግርኛ ቃል ሲኖረው፤ መጽሐፉ የሚደመደምበት ቃልም ጭምር ነው፡፡

መጽሐፉ የደርግ መንግሥት ‹‹የኤርትራን ችግር›› ለመፍታት ባካሄደው የቀይ ኮከብ ዘመቻ ወቅት የጋዜጠኝነት ሙያ ግዳጁን ለመወጣት ዘመቻውን የተቀላቀለ ጋዜጠኛ ላይ ያተኩራል፡፡ በዓሉ ራሱ በመጽሐፉ እንደሚመሰክረው የጸጋዬ ኃይለ ማርያም ቁንጽል ታሪክ ነው፡፡
ታሪኩ ከመጀመርያ መደብ አንጻር በራሱ በጸጋዬ ሲተርክ፤ መኃል መኃል ላይ ደግሞ ‹ደራሲው› በሶስተኛ መደብ ጸጋዬ ማየት የማይችላቸውን እና መገኘት የማይችልባቸውን ቦታዎች ይተርካል፡፡ ይህም በአብዛኞቹ ደራሲዎች ያልተለመደ ከመሆኑም ሌላ የጸጋዬን አስተሳሰብ እና ስሜትን መረዳት ሳይጎድልብን ሌሎች ገጸ ባህርያትና ሁነቶች ጋር በደንብ እንድንተዋወቅ ይረዳናል፡፡

መቼቱን 1974 ዓ.ም. በተለያዩ የኤርትራ ከተሞች ይበልጡን ግን በአስመራ ያደረገው ኦሮማይ በመጀመርያዎቹ ጥቂት ገጾች ብቻ አዲስ አበባ ይነካል፡፡

በቀይ ኮከብ ዘመቻ ላይ የተሳተፉ ባለስልጣናትን፣ ወታደሮችን፣ ‹ገንጣይ አስገንጣይ› ተብለው የተፈረጁ ቡድኖችን እንዲሁም የህዝቡን ስነልቦና በጥልቀት የሚዳስስ ነው፡፡ የጦርነትን መራርነትም በሰፊው ያወሳል፡፡ ከፖለቲካዊ እና ታሪካዊ ጎኑ በተጨማሪ ዘመን ተሻጋሪ የሆነውን የጸጋዬ የፍቅር ታሪክ የተተረከበትም ነው፡፡ ጸጋዬ በአዲስ አበባዋ ሮማን እና በአስመራዋ ፊያሜታ መካከል የፍቅር አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ ሲሰቃይ ይታያል፡፡ አንዳንድ የስነ ጽሁፍ ባለሙያዎች ይህ አጣብቂኝ የማዕከላዊ መንግስት ከኤርትራ ጋር የነበረውን ቁርኝት እና እልህ ሁለቱንም ሊያሳጣው እንደሚችል የሚያሳይ ፈሊጥ ነው ይላሉ፡፡

ኦሮማይ በታተመ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ባለስልጣናትን በማጋለጥ እና የአብዮቱን ስም በማጉደፍ በሚል ምክንያት ከህትመት ታገደ፡፡ በወቅቱ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ሰራተኛ የነበረው በዓሉ ግርማም ከስራው ተሰናበተ፡፡ እነኚህ ሁሉ በሆኑ በጥቂት ጊዜያት ውስጥም በዓሉ ግርማ በወጣበት ቀረ፡፡ እስከዛሬም ምስጢሩ አልተፈታም፡፡
ኦሮማይ ግን ከስምንት የእግድ ዓመታት በኋላ በ1984 ዓ.ም. በድጋሚ ለህትመት በቃ፡፡ እስከዛሬም እየታተመ እና እየተነበበ ነው፡፡ በተነበበ ቁጥር አዲስ ነው፡፡ አንዳንዴ ስለፍቅር ሌላ ጊዜ ስለጦርነት ሌላ ጊዜ ስለሐገር ደግሞ ስለታማኝነት ደግሞ ስለመገፋት እና ሀዘን ብቻ ብዙ ብዙ ሐሳቦች ያነሳል ይጥላል፡፡

ከሐሳቦች በተጨማሪ የከተሞቹን ውበት እና የሰውን አኗኗር በሚገባ የሚያስረዳ መሆኑ በአእምሮ ምስል ከሳች ነው፡፡ በርካቶች የኤርትራን ምድር ባይረግጡ እንኳ ምስጋና ለኦሮማይ ይሁንና ስለ ኤርትራ ድባብ ሐሳብ አላቸው፡፡

የስነ ጽሁፍ ውበቱን ረጃጅም ውይይቶች እና ስብሰባዎች እንደሚያደበዝዙት አይካድም፡፡ በአንድ ልብወለድ ውስጥ መገኘቱን ማመን እስከሚያቅተን ድረስ የሚያሰላቹ ፕሮፓጋንዳዎች እና ንግግሮች አሉት፡፡ ደራሲው ወቅቱን በትክክል ለመግለጽ ያደረገው ጥረት ቢሆንም መጽሐፉን ጠየም እንዳደረገው ግን አሌ የማይባል ሐቅ ነው፡፡
ከሁሉ በላይ ኦሮማይን ኦሮማይ ያደረገው ግን እውነት ማከሉ ነው፡፡ ባንወደውም ልንቀበለው ባንፈልግም ገሀዱ ፍጥጥ ብሎ ይታያል፡፡ እውነት መሆኑም ጭምር ነው በዓሉ እንዲሰወር ያደረገው፡፡ ምናልባት አንባቢዎች ሐቁ ልቧን ስብር እንዳደረጋት እንደ ሮማን ወይም አንደ ጸጋዬ ነን፡፡ ኦሮማይ ሕይወትን ያክላታል::
2 reviews
May 20, 2018
This is amazing book.i would recommend to my friends
1 review
September 6, 2023
ማንኛውም ሰው ስለ ጦርነት ያለውን ጉዳት በግልፅ የሚያሳይ መፅሀፍ ያላነበበው ሊያነበው ይገባል ::
1 review
Want to read
July 27, 2024
betam arif new eyedgemikut new
This entire review has been hidden because of spoilers.
Profile Image for Yeabnat Solomon.
46 reviews1 follower
December 25, 2024
4.5⭐
I've already been spoiled...sad. I love the writing, the characters, the politics and everything in between.
1 review
Read
April 4, 2025
Release
This entire review has been hidden because of spoilers.
9 reviews
January 5, 2026
Genius writer the fact that he wrote these is amazing he is so smart the way he told reality with fiction is amazing I really liked it
Profile Image for Mustefa.
8 reviews
September 30, 2018
I’m very excited to read
Shame on me still I didn’t read Oromay kkk
But finally...
1 review
Read
October 3, 2017
i entaras and iove this book
This entire review has been hidden because of spoilers.
Displaying 1 - 30 of 30 reviews

Can't find what you're looking for?

Get help and learn more about the design.