Jump to ratings and reviews
Rate this book

ወሪሳ

Rate this book
አንድ የአማርኛ መምህር ከአርሲ ነገሌ በሰራ ቅያሪ አዲስ አበባ ወደምትገኝ ወሪሳ በምትባል ሰፈር አክስቱ ለጊዜው ወዳወረሱት ቤት ይገባል:: መምህሩ በዚህች ሰፈር እንዲሁም በጎረቤት ሰፈሯ "እሪ በከንቱ" የሚያጋጥመውን የመላመድና የመኖር ፈተና ፣ ግጭት ፣ መስማማት ፣ ተንኮል ፣ ፍቅር ፣ አጣብቂኝ ፣ ውዝግብ ፣ እንዲሁም የሚሰማቸውን ወግና ታሪክ(ተረት) ይተርካል::

መፅሐፉ የሚያነሳችው ወጎች ፣ ተረትና ምሳሌዎች ፣ ታሪኮች(ተረቶች) ተምሳሌያዊነትን ያዘሉ ሲሆን የኢትዮጵያን ያለፈ እና የአሁኑን ታሪክ: የአሁኑ ትውልድ የሚያይበትን የተዛባ ዓይን ፣ በአሁኑ ትውልድ ውስጥ ስላሉት የተለያዩ ነባራዊ ሐቆች እንዲሁም ልዩነት ያላቸው ተጎራባቾች ላለፈው ታሪክ የሚያድርጉትን ሽሚያ እና ሽኩቻን ያሳያል::

240 pages, Paperback

First published July 14, 2015

12 people are currently reading
431 people want to read

About the author

ዓለማየሁ ገላጋይ

12 books89 followers
ፀሐፊ እና ሐያሲ ዓለማየሁ ገላጋይ በ1960 ዓ.ም አራት ኪሎ አካባቢ ተወለደ፡፡ በዳግማዊ ምኒልክ 1ኛ ና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተምሯል፡፡ በአዲስ አበባ ስኩል ኦፍ ጆርናሊዝም ተምሮ ተመርቋል፡፡

ዓለማየሁ ገላጋይ በተለያዩ ጋዜጦች ላይ በሚያቀርባቸው መጣጥፎች እና ሂሶች ይታወቃል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ፤ “አጥቢያ” ፣ “ቅበላ” ፣ “የስብኃት ገ/እግዚአብሔር ሕይወትና ክህሎት” ፣ “ኢህአዴግን እከሳለሁ”፣ “የፍልስፍና አፅናፎት”፣ “መልክአ ስብሐት” ፣ “ኩርቢት” ፣ “የብርሃን ፈለጎች” እና "ወሪሳ" የተሰኙ መፅሃፎችን ለህትመት አብቅቷል::

Ratings & Reviews

What do you think?
Rate this book

Friends & Following

Create a free account to discover what your friends think of this book!

Community Reviews

5 stars
33 (50%)
4 stars
16 (24%)
3 stars
13 (20%)
2 stars
1 (1%)
1 star
2 (3%)
Displaying 1 - 4 of 4 reviews
Profile Image for Theodros Atlaw.
7 reviews25 followers
December 4, 2021
እንደ ግሩም ግጥም፣ በተነበበ ቁጥር ሌሎች ትርጓሜዎችን የሚያነቃው፣ ሌሎች ትዝታዎችን የሚቀሰቅሰው፣ ሌሎች ስሜቶችን የሚያባንነው “ወሪሳ”፣ የዓለማየሁ ከቀድሞው/ከነባሩ ሥነ ጽሑፍ የተለየ ነገር የመስጠት ጠባይ ይበልጥ በርትቶ የታየበት ድርሰት ነው፡፡ በዚህ ድርሰት ዓለማየሁ እንደ ጋብሬል ጋርሺያ ማርቆስ፣ እንደነ ሁሊዮ ኮርታዛር፣ ምትሃታዊ እውነታዊ/Magic realist ሆኖ ይመጣል፤ እንደ ፋንታሲ ደራሲዎች ከእውናዊው ዓለም የተለየ የአሰፋፈር፣ የአኗኗር፣ የአስተዳደር ደንቦች ያሏቸውን ምናባዊ መቼቶችም ይሰጠናል፡፡
የ“ወሪሳ” ታሪክ የሚከናወንባቸው መቼቶች፣ የዘራፊዎቹ ምድር ‘ወሪሳ’ እና የፀበኞቹ ምድር ‘እሪ በከንቱ’ በጠላትነት የሚተያዩ ተጎራባች መንደሮች ናቸው፡፡ የእነዚህ ዓለማት እውነታ ከምንኖርበት ዓለም እውነታ የተቀዳም ቢሆን፣ የአንድ ማኅበረሰብ መለያ ሆኖ ሲመጣ ግን ቢያንስ የኛ እውነታ ነው ብለን ከምናምነው ጋር ይማታብናል፡፡ ወሪሳዎች የሌብነትን፣ የነጣቂነትን፣ የዘራፊነትን ትክክለኛ ማኅበራዊ እሴትነት እያጸደቁ፣ እሪ በከንቱዎች ደግሞ ወንድ ልጅ ካልተጣላ፣ ካልገደለ፣ ካልተካሰሰ ... ምኑን ወንድ ሆነው የሚል ማኅበራዊ እሴት እያወደሱ የሚኖሩ ናቸው፡፡
በእኔ ንባብ “ወሪሳ” ተቀጣጣቢ (Parodist) ድርሰት ነው፤ ታሪካችንን፣ ፖለቲካችንን፣ ማኅበራዊ ግንኙነታችንን፣ ትምህርታችንን በተውላጠ ታሪኮች (Alternate History) እንደአዲስ እንድናየው፣ እየሳቅን እንድንሳቀቅበት፣ መጪውንም እንድንፈራው ያደርገናል፡፡ በ“ወሪሳ” የአለማየሁ ገላጋይ ቀልድ አዋቂነት፣ በቋንቋ እንዳሻው የመጫወት ብቃት፣ የተረት (የተውላጠ ታሪክም ጭምር) ፈጣሪነት አቅም የታየበት ድርሰት ነው፡፡
Profile Image for Leyu.
7 reviews
August 17, 2015
መውጣት የማይቻልበት፣ ቀማኛነት የሰፈነበት ፣ እውነቱ-ውሸት ውሸቱ-እውነት የሆነበት "Dystopian" ዓለም/አካባቢ የተሳለበት ነው:: ከሁሉም በላይ የተለያዩ ያለፉ ታሪኮች በተለያዩ ስዎች ሲነገሩ ያላቸው ተምሳሌያውነትና ሊሰጣቸው የሚችለው የተለያየ ትርጉም ብዙ የሚሄድበት ነው::
20 reviews
December 28, 2020
የዚህን መፅሃ የአፃፃፍ ዘይቤ በጣም ወድጄዋለሁ። የሚገርም መሳጭነት ያለው መፅሃፍ ነው
Displaying 1 - 4 of 4 reviews

Can't find what you're looking for?

Get help and learn more about the design.