Jared Donis339 reviews59 followersFollowFollowDecember 28, 2021‘ከዕለታት ግማሽ ቀን’ የሚለውን ስራውን ከጨርስኩ በኋላ ነው ለመጀመርያ ግዜ ዶክተር አሸብርን ፈልጌ ያነበብኩት። አሌክስ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሕይወታችንን አጉልቶ በማሳየት እንደማይታማ ተደጋግሞ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው። ‘ዶክተር አሸብር’ ውስጥ ያሉት ታሪኮችም በዚህ ክህሎቱ አሌክስን በሰፊው ያስተዋወቁን የበኩር ስብስቦቹ ናቸው። አብዛኞቹን ፌስቡክ ላይ እንዳስነበበን አስታውሳለሁ፤ በደጉ ዘመን። ያው እንግዲህ አብዛኞቹ በስብከት የታጨቁ፣ ጥቂቶቹ ደግሞ ከፌስቡክ በዘለለ ለሕትመት መብቃት የሌለባቸው ስራዎች ቢኖሩበትም የአብዛኞቹን አጨራረስ በማራኪ መንገድ ስላቀረበው የማንበብ ፍላጎቴን አልቀነሰውም። በተረፈ ‘ዶክተር አሸብር’ን አንብቦ ‘ከዕለታት ግማሽ ቀን’ን ያነበበ ሰው አሌክስ ምን ያህል ራሱን እንዳሻሻለ ይገነዘባል። እኔም ወደ ኋላ ተመልሼ የመጀመሪያ ስራውን ያነበብኩት ያንን ለማረጋገጥ ነው። ለውጥማ አለ! መልካሙን ሁሉ ለአሌክስ እመኛለሁ። አብርሃም ከሚለው ገጸ ባህሪው ወጥቶ ሌሎች ወጥ ስራዎችን እንደሚያበረክትልንም ተስፋ አደርጋለሁ።
Siket Terefe68 reviewsFollowFollowJuly 4, 2026I used to hate short story books but these book changed my mind it is so funny and amazing I really loved it.
Estifanose Sahilu10 reviewsFollowFollowApril 17, 2026Read this when i was in 6th grade and re-read it several times later. Banger of a book every time!amharic favorites