Jump to ratings and reviews
Rate this book

ወንጀለኛው ዳኛ

Rate this book

Unknown Binding

39 people are currently reading
1047 people want to read

About the author

ሀዲስ ዓለማየሁ

5 books279 followers
ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (ሃዲስ ኣለማየሁ) ከአባታቸው ከቄስ ዓለማየሁ ሰለሞን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ደስታ ዓለሙ በደብረ ማርቆስ አውራጃ በጎዛመን ወረዳ በእንጾር ኪዳነ ምኅረት ቀበሌ በጥቅምት ፯ ቀን ፲፱፻፪ ዓ.ም. ተወለዱ። ገና በጨቅላ እድሜያቸው በቤተ ክርስቲያን የሚሰጠውን ትምህርት በቤተሰባቸው አጠገብና ባባታቸው አገር ደብረኤልያስ ሄደው የግእዝ ትምሕርት ቤት ቅኔ ተቀኝተዋል። የቤተክርስቲያን ስርዐታትንና መንፈሳዊ ትምህርትን በጎጃም ገዳማት በደብረ ኤልያስ፣ በደብረ ወርቅና በዲማ ከቀሰሙ በኋላ ወደ በ፲፱፻፲፰ ዓ.ም. አዲስ አበባ በመሄድ በስዊድን ሚሽነሪ ትምህርት ቤት በኋላም በራስ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከታተሉ። ለትንሽ ጊዜ በአስተማሪነት ሥራ ተሰማርተው እንዳገለገሉ የፋሽስት ጣሊያን ወረራ ተከሰተ።

የኢጣልያ ወረራ ሲከሰት ከልዑል ራስ ዕምሩ ኃይለ ሥላሴ ጦር ጋር በምዕራብ ኢትዮጵያ በአርበኝነት ሲዋጉ ቆይተው በመያዛቸው ጣሊያን ከልዑል ራስ ዕምሩ ጋር በግዞት ለሰባት ዓመታት በፖንዞ ደሴትና በሊፓሪ ደሴት ታስረው ቆይተዋል።

ከዚያም የተባባሪ ኃያላት ወታደሮች በ1935 ዓ.ም. ሲያስመልጧቸው በተመለሱበት ጊዜ በትምህርታቸው እንደገና በኦክስፎርድ ከገፉ በኋላ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት በተለይም በትምህርት ሚኒስቴር ለረጅም ጊዜ አገልግለዋል።

ሀዲስ ዓለማየሁ በርካታ የስነጽሑፍ ሥራዋችን አበርክተዋል። ከነዚህም ውስጥ ታላቅ አድናቆትንና እውቅናን ያተረፈው ሥራቸው ፍቅር እስከ መቃብር (1958) በሁለት የተለያዩ መደቦች ውስጥ የሚገኙ የሁለት ሰዎች የፍቅር ታሪክ ላይ ሲያተኩር፤ በጊዜው የነበረውን ወግና ልማድ ይገልጻል። እንዲሁም በ1970 ወንጀለኛው ዳኛ በ 1980 ደግሞ ስለ ማህበራዊ ጉዳዮችና ስለ ጣሊያን ውርስ የሚዳስሰውን የልም እዣት የተሰኙትን ልብ ወለድ ታሪኮች ለንባብ አቅርባዋል።

ከዚህ ባሻገር:

የአበሻና የወደኋላ ጋብቻ - ተውኔት
ተረት ተረት የመሰረት
ትዝታ
የተሰኙት ጽሁፎችና የሌሎች በርካታ ሥራዎች ባለቤት ናቸው።

ሀዲስ ዓለማየሁ በኢትዮጵያ የስነ ጽሑፍ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽዖ በማበርከታቸው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዶክቶርነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል። ደራሲው በኅዳር 26 ቀን 1996 ዓ.ም. በ94 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

Ratings & Reviews

What do you think?
Rate this book

Friends & Following

Create a free account to discover what your friends think of this book!

Community Reviews

5 stars
38 (45%)
4 stars
19 (22%)
3 stars
11 (13%)
2 stars
7 (8%)
1 star
8 (9%)
Displaying 1 - 7 of 7 reviews
Profile Image for Zola.
16 reviews2 followers
June 9, 2022
ይህ መፅሐፍ በውስጡ እጅግ ቁም ነገሮችን ታሪኮችን ትውፊቶችንና ፍልስፍናዎችን ታጭቋል ፣ በኢትዮጲያን በአፄው ስርዓት በነበረበት ወቅት የነበረውን ሹመኞት በህዝብ ላይ የሚያደርሱትን የህዝብ ሰቆቃ ፍንትው አድርጎ ለማሳየት ይሞክራል። ይህ መፅሐፍ 'ቄሳርና አብዮት' የተሰኘው የብርሃኑ ድንቄ መፅሐፍ ጋር በተዘዋዋሪ ይገናኛል። ለዚህም ማስረጃ ቀኝ አዝማች ዳኛቸው ፍሪሳ የተባለው character በቂ ነው።ህዝብ ፍትህን ከፈጣሪና ከፍርድ ቤት ሲያጣ ምን ያድርግ? ምንስ ያደርጋል? አንብቡት! ወንጀለኛው ዳኛ በተወሰነ መልኩ የUtiltorianism ፍልስፍና የሚታይበት ማለትም ድርጊቶች ትክክል ወይም ስህተት የሚሆኑት በውጤታቸው እንጂ መጥፎ ወይም ጥሩ ተብሎ የተቀመጠ ሞራል በራሱ እንደሌለ የሚሞግት መፅሐፍ ነው። የታሪክ መዋቅሩና አፃፃፉ እጅግ የሚማርክ ነው። የጥላሁን ድርጊት በተወሰነ መልኩ የ 'Crime and punishment' main character Raskonlnikov ጋር የሚመሳሰል ብዙ ነገር አለው።
ገራሚ መፅሐፍ ነው ያላነበባቹ አንብቡት:) ያነበባቹ ድገሙት:) I don't know If I write any spoilers or not the book has 583 pages:)
1 review
Read
December 20, 2019
መፅሃፉ በርግጥም በፊት ተፅፈው ዛሬም ተወዳጅ ሆነው ከዘለቁ መፅሀፍት መካከል አንዱ ነው፡፡
1 review
February 3, 2017
i want to read this amazing book
This entire review has been hidden because of spoilers.
Displaying 1 - 7 of 7 reviews

Can't find what you're looking for?

Get help and learn more about the design.