Jump to ratings and reviews
Rate this book

ዐፄ ዮሐንስና የኢትዮጵያ አንድነት

Rate this book
አፄ ዮሐንስ ለኢትዮጵያ አንድነት ያደረጉትን ታላላቅ ክንውኖችና አስተዋፅዎችን የከፈሉትን ታላቅ መስዋትነት የከተበ ትልቅ የታሪክ መጸሐፍ።

Paperback

25 people are currently reading
653 people want to read

About the author

ተክለጻድቅ መኩሪያ

4 books19 followers
ተክለጻድቅ መኩርያ በ 1906 ዓ.ም. በተጉለትና ቡልጋ አውራጃ አሳግርት ልዩ ስሙ ሳር አምባ በተባለ ሥፍራ ተወለዱ።

ዕድሜያቸው ለትምሕርት ሲደርስ መጀመሪያ ከአባታቸውና ቀጥሎም በአጥቢያቸው ባህላዊውን ትምሕርት እስከቅኔ ያለውን ቀስመዋል። ከዚያም አዲስ አበባ መጥተው አሊያንስ ፍራንሴዝና ተፈሪ መኮንን ትምሕርት ቤት ገብተው የጊዜውን የትምሕርት ደረጃ አጠናቀዋል።

ኢጣልያ አገራችንን የወረረች ጊዜም በየካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. ፍጅት ተይዘው ወደ ሶማሌ ደናኔ ተግዘው ለሦስት ዓመታት ታስረዋል። ከነጻነትም መልስ አገራቸውን በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች አገልግለዋል።

መጀመሪያ ተቀጥረው ያገለገሉት በትምሕርትና ሥነጥበብ ሚኒስቴር ነበር። እዚያም ሳሉ በአገራችን ሰው የተጻፈ የአገራችን ታሪክ አንድም ባለመኖሩ በቁጭትና በመቆርቆር ነበር ‘መጻፍ አለብኝ’ ብለው በደንብ ከሚታወቀው ከቅርቡ ጊዜ በቅጡ ወደማይታወቀው የሩቁ ዘመን መጻፍ የጀመሩት። የመጀመሪያውን መጽሐፍ “የኢትዮጵያ ታሪክ ከዓፄ ቴዎድሮስ እስከ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ” የሚለውን በ 1938 ዓ.ም. አሳተሙ። ከጫፍ እስከ ጫፍ ጽፈው የመጨረቻውን መጽሐፍ፣ የታሪካችን መጀመሪያ የሚሆነውን “የኢትዮጵያ ታሪክ ኑብያ-አክሱም-ዛጉዬ እስከ ዓፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት” የሚለውን በ1951 ዓ.ም. አቅርበዋል። እኒህኑ መጻሕፍት ትምሕርት ሚኒስቴር ታሪክ ለማስተማሪያ በትምሕርት ቤት ተጠቅሞባቸዋል።

ተክለጻድቅ ከታሪክ ውጭ የጻፏቸው “የሰው ጠባይና አብሮ የመኖር ዘዴ” እና በሚዮቶሎዢያ (mythology) ላይ ያተኮረ “ከጣዖት አምልኮ እስከ ክርስትና” የሚሉም መጽሐፎች አሏቸው።

ተክለጻድቅ በምድር ባቡር በዋና ጸሐፊነት፥ በቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ዋና ሥራ አስኪያጅነት፥ እንዲሁም በፈረንሳይ፥ በእስራኤል፥ በዩጎዝላቪያ በዲፕሎማሲ ሥራ በመጨረሻም የትምሕርትና የባህል ሚኒስቴር ሆነው አግልግለዋል። በፈቃዳቸው ጡረታም ከወጡ በኋላ በምርምር የታገዙ ሦስት ታላላቅ የታሪክ ሥራዎችን አቅርበዋል።

ተክለጻድቅ ከረጅም የአገልግሎት ዘመን በኋላ በተወለዱ በ ሰማንያ ስድስት ዓመታቸው ሐምሌ 16 ቀን 1992 ዓ.ም. አርፈዋል።

የተክለጻድቅን ሥራዎች ዋጋ የምንሰጣቸው ለሚከተሉት ምክንያቶች ነው፦

• ታሪክን ከተተበተበበት ልማዳዊ አጻጻፍ ነጻ አውጥተው በሰገላዊ መንገድ መጻፍ በመጀመራቸው

• አገራዊውን መረጃም ሳይተው በውጭ ቋንቋ በጣልያንኛ፥ በፈረንሳይኛ፥ በእንግሊዝኛ ጭምር ያለውን ሁሉ ተጠቅመው ከስር እስከጫፍ የአገሪቱን ታሪክ በመጻፋቸው

• እኒህን ሁሉ መጻሕፍት የጻፉት በመደበኛ የቀለም ትምሕርት ቤት ሳይሰለጥኑ፥ በከፍተኛ የመንግሥት ሥራና ኀላፊነት ተጠምደው፥ ያላቸውን የምዝናኛ ጊዜ ሁሉ ሰውተው ቁም ነገር በመሥራታቸው

• በተለይም ከአሥራ አምሥት ዓመታት በላይ የደከሙበት “የግራኝ አሕመድ ወረራ” የተሰኘው መጽሐፋቸው በመቶ አምሳ አምሥት ምዕራፎችና ስምንት መቶ አርባ ገጾች በጽሑፍ፥ በካርታ፥ በሠንጠረዥ፥ በፎቶግራፍ መረጃዎች ተሞልቶ ሥርዓት ባለው መልክ ታሪኩ ትንትን ተደርጎ የተሠራ ግዙፍ ሥራ በመሆኑ

Ratings & Reviews

What do you think?
Rate this book

Friends & Following

Create a free account to discover what your friends think of this book!

Community Reviews

5 stars
18 (56%)
4 stars
6 (18%)
3 stars
6 (18%)
2 stars
1 (3%)
1 star
1 (3%)
Displaying 1 - 3 of 3 reviews
Profile Image for Getachew desalegn.
3 reviews6 followers
January 4, 2019
This book is the kind of encouraging to know your country more and more. After I have read this book I want to know situations beside the king Yohannes iv ... i have read the history of ETHIOPIA before and after Emperor Yohannes, the contributions of this patriot king, finally he was sacrificed to his country while fighting against Dirbush(Sudan) in Mettema I were interested in the reading of this book in general.
Displaying 1 - 3 of 3 reviews

Can't find what you're looking for?

Get help and learn more about the design.