Martha H. Kidane46 reviews30 followersFollowFollowSeptember 18, 2015ጥዑም በመጽሀፉ የተመስገንን ታሪክ እያዋዛ አንባቢውን የታሪኩ አንድ አካል አድርጎ ከላሊበላ በሰንደጋ ደብረ ታቦርን አቋርጦ በደብረማርቆስ በኩል በወግ ሽርሽር ወደ አዲስ አበባ ይወስደናል:: በገጸባህርያቱ ጀርባ ጎራ አስለይቶ ያፋልመናል:: ከባለታሪኩ ጋር ጥሎ ከባለታሪኩ ጋር ያነሳናል:: የሕይወትን ውጣውረዶች የኑሮን የተለያዩ ገጽታዎች እኛን በሚመስሉ እንደ እኛ በሚናገሩ የራሳችንንም ዓይነት የሕይወት መርህ እና እምነት ባነገቱ ገጸባህርያት በኩል የራሳችንን ጥዑም ታሪክ ያስነብበናል::
Tioum Meaza1 reviewFollowFollowReadAugust 31, 2021ገዐረ- ያልታጠበ አልማዝ---,, በሚል ርእስ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ጽፎ ነበር.. አልማዝ ሲጠረግ ዉበቱ እንደሚያበራ ሁሉ ገዐረ ሲነበብ ድንቅ ነው በማለት ነበር የዘጋው፡፡ Dራሲው ከገፀ-ባህሪያቶቹ ስር ሁኖ የፃፈው ነው የሚመስለኝ- ሲል ፀሀፊ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ በአንድ መድረክ ተናግሮ ነበር፡፡ ፋና 98.1 ሲተረክ ከ33 ሺ በላይ ስልኮች ለጣቢያው ተደውለው በሪከርድነት ተነግራል....