Jump to ratings and reviews
Rate this book

ከደንቢያ - ጎንደር እስከ ዋሽንግተን ዲሲ

Rate this book

211 pages, Paperback

First published January 1, 2009

1 person is currently reading
99 people want to read

About the author

አስማማው ኃይሉ

4 books9 followers
ደራሲ አስማማው ኃይሉ ከአባቱ ከአቶ ኃይሉ ጓንጉል እና ከእናቱ ከወ/ሮ ዓለሚቱ ገረመው ሐምሌ 8 ቀን 1947 ዓ.ም (እ.ኤ.አ ጁላይ 16 ቀን 1955 ዓ.ም) ጎንደር ከተማ ተወለደ፡፡ እዛው ጎንደር ከተማ በሚገኘው የቀድሞው ቀ.ኃ.ስ. 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እስከ 12ኛ ክፍል ተምሮ ወደ አዲስ አበባ ከተማ በመምጣት በ1966 – 1969 ዓ.ም በስታስቲክ መስሪያ ቤት ሠራተኛነት ተቀጥሮ በበርካታ የሃገሪቱ ክፍሎች ተዘዋውሮ ሠርቷል፡፡

በወቅቱ ማለትም በ1966ዓ.ም በኢትዮጵያ የተቀጣጠለውን ሕዝባዊ አመፅ በመቀላቀል “የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ” (ኢ.ህ.አ.ፓ) አባል በመሆን በሕቡዕ የፖለቲካ ትግል አካሂዷል፡፡ በአምባገነኑ ወታደራዊ መንግሥት ዕመቃ የከተማው ትግል ሲታፈን “የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ሠራዊትን” (ኢ.ህ.አ.ሠ) በመቀላቀል ለትጥቅ ትግል ወደ አሲምባ አምርቷል፡፡

ከወታደራዊ ሥልጠና በኋላም በበለሣ፣ በጭልጋ፣ በአርማጭሁና በሌሎች የገጠር ስፍራዎች በመሰማራት የሕይወት መስዋዕትነት በሚጠይቀው ትግል ውስጥ በቆራጥነት ተሳትፏል፡፡ ደራሲ አስማማው በተለይ የገጠሩን አርሦ አደሩን በማታገል ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡ በዚህ ትግል ላይ እያለ የደርግ ሥርዓት አራማጆች እጅ በመውደቁ ለእስር ተዳርጎ ብዙ ድብደባ፣ ሥቃይና እንግልት ደርሶበታል፡፡

ደራሲ አስማማው ለሕትመት ከበቁ ሥራዎቹ ውጭ አንድ 230 ገፆች ያሉት ልቦለድ እና ሌላ የግጥም መድበል ጽፎ አጠናቋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ላይ መጣጥፍ በማቅረብ እንዲሁም ቃለምልልስ በመስጠት ተሞክሮውን ለማሕበረሰብ ጥቅም እንዲውል ጥረት አድርጓል፡፡

ደራሲ አስማማው ኃይሉ በድንገት የተፈጠረ የጤና እክል ሲያጋጥመው አዲስ አበባ ውስጥ የመጨረሻ መጽሐፉን ሕትመት በማዘጋጀት ላይ ነበር፡፡ በአገር ውስጥ ህክምና ቢወስድም ፈፅሞ ስላልተሸለው ለከፍተኛ ህክምና ወደ አሜሪካ በመሄድ ፊላደልፊያ በሚገኘው የፔንሳልቫንያ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ገብቶ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ እ.ኤ.አ. ረቡዕ ኦክቶበር 14 ቀን 2015 በተወለደ በ61 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡

Ratings & Reviews

What do you think?
Rate this book

Friends & Following

Create a free account to discover what your friends think of this book!

Community Reviews

5 stars
2 (66%)
4 stars
1 (33%)
3 stars
0 (0%)
2 stars
0 (0%)
1 star
0 (0%)
No one has reviewed this book yet.

Can't find what you're looking for?

Get help and learn more about the design.