Jump to ratings and reviews
Rate this book

የኤርትራ ጉዳይ

Rate this book
በዚህ ርዕስ ተጽፎ የቀረበው ታሪክ በሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የተመረኮዘ ነው፡፡

1ኛ. አብዛኛው የኤርትራ ሕዝብ ፣ ከባዕድ አገዛዝ ለመላቀቅና ወደ መሠረት አገሩ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ኢትዮጵያ ወይ ሞት ብሎ በመታገል ምን ያህል መከራና ፈተና እንደተቀበለ
2ኛ. የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ኤርትራን ከኢትዮጵያ ጋር ለማዋኃድ በአራቱ ኃያላን መንግሥታት ዳንነትና ቀጥሎ በተባበሩት መንግሥታት ሸንጎ ላይ ለብዙ ዓመታት ያደረገው ፋታ የሌለው ሙግት ምን ውጤት እንደሰጡ
3ኛ. በተባበሩ መንግሥታት ሸንጎ ላይ ኤርትራ በፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ጋር እንድትቀላቀል ፣ ፍርዱ እንዴት እንደተወሰነና፣ ከዚያም ለአሥር ዓመታት የተካሄደው የፌዴሬሽን አስተዳደር በምን መልክ ይሠራበት እንደነበረና በኃላም በምን አኳኋን እንደፈረሰ

እውነተኛውን ታሪክ የኢትዮጵያና የኤርትራ ሕዝቦች እንዲያውቁት በዝርዝር የተዘጋጀና ከፍ ያለ ጥረት የተደረገበት ነው፡

ዘውዴ ረታ - See more at: http://zewderetta.com

Paperback

30 people are currently reading
775 people want to read

About the author

ዘውዴ ረታ

3 books11 followers
አምባሳደር ዘውዴ ረታ በአዲስ አበባ ነሐሴ 7 ቀን 1927 ዓ.ም. ልዩ ስሙ ኦርማ ጋራዥ አካባቢ ተወለዱ:: ትምህርታቸውን በሊሴ ገብረማርያም ለ12 ዓመታት ከተማሩ በኋላ ወደፈረንሳይ ሀገር በመሄድ ተምረው በጋዜጠኝነት በዲፕሎማ ተመርቀዋል:: ወደሃገር ከተመለሱም በኋላ በተለያየ የጋዜጠኝነትና በዲፕሎማትነት ሙያ አገልግለዋል:: በግዜውም የወሬ ምንጭ የሚባል የዜና አገልግሎት መስርተው ከዋና ዳይሬክተርነት እስከ ረዳት ሚኒስትርነት ደረጃ ያገለገሉ ሲሆን በፈረንሳይ የአምባሳደር ምክትል፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ረዳት ሚኒስትር፣ በሮም የንጉሠ ነገስቱ አምባሳደር እና በቱኒዚያ አምባሳደር ሆነው መስራታቸው ተጠቃሽ ነው:: በደርግ የስልጣን ዘመንም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ የዓለም አቀፍ የእርሻ ልማት ፈንድ መስሪያ ቤት የመንግስታት ግንኙነትና የፖለቲካ ኃላፊ በመሆን ለረጅም አመታት አገልግለዋል::

አምባሳደር ዘውዴ ጡረታ ከወጡም በኋላ በታሪክ ተመራማሪነት እና በጸሐፊነት ታዋቂነትን ያተረፉ ሲሆኑ ያሳተሟቸው መጻህፍት፦”የኤርትራ ጉዳይ በቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት”፣ “ተፈሪ መኮንን ረዥሙ የሥልጣን ጉዞ” እና “የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት ታሪክ” ናቸው::

አምባሳደር ዘውዴ ለሥራ ጉዳይ በሄዱበት ለንደን ከተማ ድንገት በመታመማቸው በለንደን ቅድስት ማርያም ሆስፒታል ከፍተኛ የሕክምና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይተው ፣ በ80 ዓመታቸው ያረፉት መስከረም 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ነበር፡፡

Ratings & Reviews

What do you think?
Rate this book

Friends & Following

Create a free account to discover what your friends think of this book!

Community Reviews

5 stars
30 (63%)
4 stars
6 (12%)
3 stars
7 (14%)
2 stars
3 (6%)
1 star
1 (2%)
Displaying 1 - 2 of 2 reviews
Displaying 1 - 2 of 2 reviews

Can't find what you're looking for?

Get help and learn more about the design.