Jump to ratings and reviews
Rate this book

ጦቢያ

Rate this book
በኢትዮጵያ የሥነ ፅሑፍ ታሪክ የመጀመሪያ ልብወለድ መፅሐፍ ለመሆኑ የሚነገርለት ይህ መጽሐፍ በወቅቱ ተነስቶ የነበረውን የአረማውያንንና የክርስቲያኖችን ጦርነት ይተርካል። ደራሲው በመፅሐፉ ውስጥ ስለተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ማለትም ስለደግነትና ክፋት፣ ስለሀይማኖትና ፍቅር በሰፊው ያትታሉ። መፅሐፉ በተለይ የፍቅርን ሀያልነት ለማሳየትና የሀይማኖት ልዩነት ስላልበገረው ታላቅ ፍቅር በሰፊው ይተርካል። በተጨማሪም ደራሲው በጽሑፉ ውስጥ ሊያስተላልፉ የሞከሩት መልዕክት የሰው ልጅ በባዕድ አምልኮ ተሸብቦ ከመኖር ይልቅ ፈተናና ችግር ቢገጥሙት እንኳን ለእነዚህ ሳይበገር በአንድ አምላክ አምኖ ከጸና ድል ሊያደርግ እንደሚችል ነው።

90 pages, Paperback

First published January 1, 1907

6 people are currently reading
173 people want to read

About the author

አፈወርቅ ገ/ኢየሱስ በ1860 ዓ.ም ጎንደር ዘጌ በተሰኘችው ስፍራ ተወለዱ፡፡ የእቴጌ ጣይቱ ብጡል የሥጋ ዝምድና እንዳላቸው የሚነገርላቸው አፈወርቅ በልጅነት ዕድሜያቸው አዲስ አበባ መጥተው አደጉ።

ለዘመናዊት ኢትዮዽያ ሥልጣኔ መስራች የሆኑት ዳግማዊ አጤ ምኒሊክ ያውሮፓን ሥልጣኔ ቀስመው እንዲመጡ ወደውጭ ሀገር ከላኳቸው ብልህ ወጣቶች መካከል አንዱ አፈወርቅ ገ/ኢየሱስ ናቸው።

አፈወርቅ የ20 ዓመት ብላቴና ሳሉ በአጤ ምኒልክ በጎ ፈቃድ ከሁለት ወጣቶች ልጅ ጉግሳ ዳርጌ እና ልጅ ቅጣው ዛማኑኤል ጋር በ1880 ዓ.ም ወደ ስዊዘርላንድ ተላኩ። ከዚያ ከደረሱ በኋላ በገዛ ፈቃዳቸውና ባልታወቀ ምክንያት ወደ ጣሊያን ቱሪን ሄደው በኮሌጅ ኢንተርናሲዮናል ደ.ቤሊ አርቲ ከፍተኛ የሥነ ጽሑፍ ትምህርት ተከታተሉ። ከአድዋ ጦርነት በ1986 በፊት ወደ ኢትዮዽያ ተመልሰው በ1882 በቤተመንግስት ባለሟልነትና በሠዓሊነት ሙያ ያገለገሉት አፈወርቅ፥ በተለይ ከእቴጌ ጣይቱ ጋር በመቀያየማቸው በ1888 ዓ.ም. በስደት መንፈስ ወደ ኢጣሊያ ተመለሱ። በናፖሊ የምስራቅ ጥናት ኢንስቲቲዩት የአማርኛ ቋንቋ በማስተማር የፕሮፌሰርነት ማእረግ አግኝተዋል።

አፈወርቅ በኢጣሊያ ሳሉ ለኢትዮዽያ ዘመናዊ ሥነ ጽሁፍ ዕድገት የበኩር ልጅ ሊያሰኙዋቸው የቻሉትን የአማርኛ መጻሕፍት የጻፉ ሲሆን እንደገና ወደሀገራቸው በ1922 ዓ.ም. እስከተመለሱ ድረስ፥ በግእዝ፥ በአማርኛ፥ በኢጣሊያንኛ እና በፈረንሳይኛ ቋንቋዎች የመማሪያ መጻሕፍት፥ የታሪክ እና የፈጠራ ልቦለድ መጻሕፍትን አሳትመዋል።

አፈወርቅ በ1902 ዓ.ም. ሮማ ባሳተሙት ዳግማዊ ምኒሊክ በሚለው የታሪክ መጽሐፋቸው ከግዕዝ ጽሑፍ ባህል ወደ ዘመናዊ አማርኛ ኪናዊ ሥነጽሑፍ ለተደረገው ሽግግር በተለይ በ1908 ዓ.ም. በሮም ባሳተሟት ጦቢያ-ልቦለድ ታሪክ የፈጠራ ሥራቸው-በኢትዮዽያ የአማርኛ ዘመናዊ ሥነጽሑፍ መሥራች ካሰኛቸው ማእረግ ባሻገር በአፍሪካ ቋንቋዎችም ታሪክ- በሀገርኛ ቋንቋ በመጻፍ የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪካዊ የሚል ምስክርነት አግኝተዋል።

ቀደም ሲል ለሀገራቸው በአስተርጓሚነት፥ በጉምሩክ ሥራ ኃላፊነት ነጋድራስነት እና በአምባሳደርነት ሮም ያገለገሉት አፈወርቅ በኢትዮዽያና ኢጣሊያን ጦርነት ወቅት 1924 - 1933 ኢጣሊያን ወገን ሆነው በ የቄሣር መንግስት መልእክተኛነት በሀገራቸው ልዩ በደል ፈጽመዋል በሚል ከነፃነት በኋላ በ1933 የዕድሜ ልክ እሥራት ተፈርዶባቸው በጅማ ጅሬን እሥር ቤት ለ6 ዓመታት በግዞት ቆይተው፥ በእርጅና እና በጤና ማጣት መስከረም 15 ቀን 1939 ዓ.ም በ79 ዓመታቸው አረፉ።

ምንጭ:ብርሀነመስቀል ደጀኔ 2000ዓ.ም ብራና.ማ.ቤ ካሌንደር።

Ratings & Reviews

What do you think?
Rate this book

Friends & Following

Create a free account to discover what your friends think of this book!

Community Reviews

5 stars
10 (50%)
4 stars
6 (30%)
3 stars
4 (20%)
2 stars
0 (0%)
1 star
0 (0%)
Displaying 1 of 1 review
Profile Image for Theodros Atlaw.
7 reviews25 followers
Read
January 1, 2025
Published in 1908, Afäwärq Gäbrä Iyäsus's Tobia is widely considered the first Amharic novel. Originally titled Lib Wäläd Tarik (Fictional Story), the Ministry of Education and Fine Arts modernized the language and republished it in 1965/6, changing the title to Tobia after the protagonist. (Research indicates that Täklä Maryam Fantayé, a staff at the Ministry at the time, oversaw these revisions, including the title change.) The novel's original title may have contributed to the later adoption of "Lib Wäläd/Liboläd" (Novel) as a genre term for fictional narratives in Amharic.

Tobia depicts two antagonistic groups—Christians and those labeled "barbarians"—whose starkly contrasting lifestyles and beliefs fuel intense conflict. The narrative uses symbolic descriptions of their physical appearances to emphasize their perceived opposition, employing compelling narrative techniques such as vivid imagery or contrasting parallel scenes to heighten the tension. However, the narrative ultimately transcends this conflict, envisioning a unified society under a single religion and king.

Tobia remains a subject of ongoing scholarly debate and interpretation, sparking considerable discussion and analysis within Amharic literary studies. It has received both critical acclaim and criticism.
Displaying 1 of 1 review

Can't find what you're looking for?

Get help and learn more about the design.