Jump to ratings and reviews
Rate this book

የስንብት ቀለማት

Rate this book

960 pages, Paperback

First published June 25, 2016

14 people are currently reading
308 people want to read

About the author

አዳም ረታ

13 books186 followers
አዳም ረታ በ1950 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተወለደ። በትምህርት አለም - በጂኦግራፊ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተቀብሏል። ሁለተኛ (የማስተርስ) ዲግሪውን ደግሞ በውጭ ሀገር አግኝቷል። የሚፅፈው በአብዛኛው አጫጭር ልቦለዶችን ቢሆንም ግጥሞችንም ይፅፋል። በተለያዩ ጊዜያት ግጥሞቹ በተለያዩ መፅሔቶች ላይ ታትመዋል። ያልታተሙ ግጥሞችም አሉት።

‹ማሕሌት›፣ ‹አለንጋና ምስር›፣ ‹እቴሜቴ ሎሚ ሽታ›፣ ‹ከሰማይ የወረደ ፍርፍር›፣ ‹ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ›፣ ‹ሕማማትና በገና› የተሰኙ የአጫጭር ልብወለዶች ስብስብ መጽሀፍትን በግሉ አሳትሟል፡፡

የአዳም የረዥም ልብወለድ ሥራ የሆኑት ‹ግራጫ ቃጭሎች› እና ‹መረቅ›ም በብዙ አንባቢዎች ዘንድ ተወዳጅ ናቸው፡፡

አዳም ረታ በአጻጻፍ ስልቱ ልዩ፣ በቋንቋ አጠቃቀሙ ማራኪ እና በሚያነሳቸው ሀሳቦች ምጡቅ ደራሲ እንደሆነ የስነ-ጽሑፍ ባለሙያዎችና የሥራዎቹ አንባቢዎች ይመሰክራሉ፡

Ratings & Reviews

What do you think?
Rate this book

Friends & Following

Create a free account to discover what your friends think of this book!

Community Reviews

5 stars
31 (64%)
4 stars
8 (16%)
3 stars
2 (4%)
2 stars
4 (8%)
1 star
3 (6%)
Displaying 1 - 6 of 6 reviews
Profile Image for Blen.
182 reviews6 followers
July 16, 2022
Bought this book yesterday and just finished reading it. I loved it, and I can't wait to read his other books.
10 reviews2 followers
April 25, 2021
ምናለ *እነዚያ* ደራሲያንም እንደ አዳም ረታ ያለ ጭንቅላት ቢታደሉ።
ጋሽየ ብዕርህ አይንጠፍ! የዚህ ዘመን የስነ-ፅሁፍ መለኪያየ አንተ ነህ። ከሁሉም በላይ ራስህን ለሙያህ አሳልፈህ የሰጠህ ድንቅ አሰላሳይ በመሆንህ ስራዎችህ ዘመን ተሻጋሪዎች ስለመሆናቸው ምንም ጥርጥር የለኝም።
Profile Image for Jared Donis.
331 reviews58 followers
June 30, 2022
በቃ አዳም ረታ እጅግ አስደንጋጭ ደራሲ ነው! ብሶበታል! እየደነገጣችሁ የምታነብቡት መጽሐፍ የአዳምን ብቻ ነው። የስንበት ቀለማት አስደንጋጭ ድርሰት ነው። ደራሲ እንዴት በዚህ መጠን ሊጠልቅ እና ሊረቅቅ ይችላል? እንዴት በዚህ መጠን ሊያውቀን እና ሊያብራራን ይችላል? ይህንን ሊያደርግ የሚችል ተሰጥዖ ያለው አዳም ረታ ብቻ ይመስለኛል። እርሱ በምናቡ የወለዳቸውን ሕይወቶች በገሃድ ብንኖራቸው እንኳ እርሱ በጻፈበት ጥልቀት መጠን መልሰን መጻፍ የምንችል አይመስለኝም።

እንዴ?! ቀላል የህጻናት ተረት የነበረውን ስንዝሮን እንኳ ሌላ ታሪክ ውስጥ እኮ ነው የከተተው። ቴዎድሮስ ገብሬ በድህረ-ቃሉ፣ "አዳም ከተረት ዓለም የመለመለውን ስንዝሮ (መንኮብያ) ተራ የብልጣብልጥነት መለያውን (trickster character) አራግፎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅ ትዕምርት (a symbol of national imaginary)፤ የዘላለማዊነቷም ወኪል አድርጎታል (an agent of eternity)" እንዳለው፤ ከዚያም ባሻገር የድንቅ አዕምሮው የምናብ ጥንካሬን ማሳያ ነው።

‘የስንብት ቀለማት’ ልክ እንደ ስሙ ነው። አዳም ከ‘መረቅ’ ላቅ ባለ መልኩ እዚህ ድርሳን ውስጥ ያሉትን ባለታሪኮች ደመቅ ያለ የስንበት መስመር ሰጥቶአቸዋል። እንደቀደመው ድርሰቱ እገሌ ምን ሆኖ ይሆን ብለን ብዙም እንድንጨነቅ አላደረገንም። ይህ እጅግ አስደስቶኛል። በድርሰቱ እኩያኑን ገፀ-ባህሪያት በተለይም ደግሞ ኢትዮጵያን የሚጠሉትን ልካቸውን ነግሮአቸዋል። ኢትዮጲያን እና ኢትዮጵያዊነትን አለሁ አለሁ ከሚሉ ከብዙ የፖለቲካ ተንታኞች ይልቅ አድምቆ ሞግቶለታል። ይህ ጉዳይ በራሱ መጽሐፍ ይወጣዋል። የበረታ ይጻፍበት። እኔ ግን እየተገረምሁ ብቻ ዝም ልበል።

አዳም በሚጽፍበት ዘመን ተወልጄ ስራዎቹን ማንበብ በመቻሌ ለፈጣሪ ተጨማሪ ምስጋና አቀርባለሁ! ኖቤል መሸለም ያለበት ደራሲ ነው ይህ ሰው! አዳም ረታ፣ አንድዬ ረጅም ዕድሜ ከማይነጥፍ ብዕር ጋር ይስጥህ! አንተ በሳልካት ኢትዮጵያ ውስጥ እኛ ባይሳካልን ልጆቻችን ለመኖር ይብቁ!
5 reviews
Read
January 25, 2024
This book has the theme of such books as Norwegian wood, the death of ivan illych, and so on. It has a zen side to it because, it lets you sit with as much detail as possible and you sort of lose purpose or destination. You just read for the sake of reading.
Displaying 1 - 6 of 6 reviews

Can't find what you're looking for?

Get help and learn more about the design.