Martha H. Kidane46 reviews30 followersFollowFollowMarch 21, 2018ቀልብን የሚስበው የዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ የአተራረክ ስልት የለመድነውን ገጸባህርይ ሲሳይን በሶስተኛ መደብ ትርክት ይዞልን ቀርቧል:: በዚህ መጽሀፋቸውም ሲሳይን ተከትለን ከአንዱ ከተማ ወደሌላው ከጢያራ ወደ መኪና እንዲሁም የእግር ጉዞን እየተጠቀምን እንድንዘዋወር በከተሞቹ እንድንደመም ሕዝቦቹንም ከነባህርያቸው እንድንረዳቸው አድርገውናል:: በዶ/ር ዓለማየሁ መጽሀፍ እንደ አንባቢ ሳይሆን ልክ እንደ አንድ ረዳት ገጸባህሪ ከሲሳይ ጋር እየዳከርን አንዳንዴም "እንደው ምን ስል ነው እዚህ ውስጥ የገባሁ?" ብሎ ሲቆጭ አብረነው "እንግዲህ አንዴ ገብተንበታል እንዝለቅ" በሚል ስሜት ከገጽ ወደ ገጽ አብረን እንድንጓዝ በማድረግ ሀገራችን ያላትን ጸጋ እንድንደነቅበት፣ ጥቅም ላይ ስላላዋልነው እንድንቆጭበት እንዲሁም እራሳችንን "እኔስ?" ብለን እንድንጠይቅ ትልቅ እድል ከፍተውልናል:: በዚህ መጽሐፍም በአንባቢው ላይ ጥያቄን የሚያጭሩ ብዙ ክስተቶች ያሉ ሲሆን እንደ ግለሰብም "እኔ ብሆንስ ምን አድርግ ነበር?" የሚል ተፈተሻዊ ጥያቄን የሚያጭሩ ናቸው:: 'ቅርስ ለማን ነው የሚገባው?' የሚለውንም ክርክር፤ ባለቤትነትን በኃይል ሳይሆን እንዴት በስልት ማስከበር እንደሚቻል ሲሳይና ናታሊያን በተቃራኒ ጎራ ለይተው ልብ ሰቃይ የሆነ ፍልሚያን እንድንታደም ይጋብዙናል:: ዶ/ር ዓለማየሁ በዚህ መጽሐፋቸው እንደቀደመው ጊዜ ሁሉ የእምነት ቦታዎችን እና ሀይማኖታዊ ቅርሶችን ማእከል አድርገው ጽፈዋል:: በዚህኛው መጽሐፋቸውም ወደ ጣና ገዳማት ሲወስዱን ወቅታዊ ትኩሳት የሆነውን የጣና ሀይቅን ጉዳይ ጉዳዬ ብለን እንድናጤነው እና ትክክለኛውን መፍትሄ እንድንዘይድ ትኩረታችንን በሲሳይ ቁጭት በኩል እንድንሰበስበው ያነቁናል:: እርግጥ ይህ መጽሐፍ እንደ ቀደሙት ሁለት መጽሐፍት ሁሉ የገዘፈ እና ለረጅም ጊዜ ከውስጥ የማይወጣ ጥያቄን ያስቀምጣል:: እኔ በበኩሌ ያቺ ጣናን ተከትላ የምትመሰረተው ከተማ ሕልም እውን እንዲሆን ምኞቴ ነው:: ለዚህኛውም መጽሐፍ እንደቀደሙት ሁሉ ማሳሰቢያውን መድገሙ አስፈላጊ ይሆናል "አፋጣኝ ሥራ ካላችሁ እንዳትጀምሩት"::
Addisalem Mitiku4 reviews1 followerFollowFollowReadDecember 14, 2019I can't pass not appreciating the author
Sosna Dawit1 reviewFollowFollowJanuary 29, 2020Owww beeetam des mil book new yewnet betam betam arif new ye dngel lij kefith yikum tnk u
Um Lij1 reviewFollowFollowWant to readOctober 26, 2020goodThis entire review has been hidden because of spoilers.
Teshome1 reviewFollowFollowFebruary 28, 2019Down loadingThis entire review has been hidden because of spoilers.
Getachew desalegn3 reviews6 followersFollowFollowJanuary 3, 2020መርበብት ስለሃገራችን ኢትዮጵያ በተለይም ስለኦርቶዶክስ ሃይማኖት ብዙ ሚስጥሮች የሚያትት ድንቅ መጽሃፍ ነው። በታሪኩ ሲሳይ ከጣሊያናዊው የካቶሊክ ሚስተር እስጢፋ የተቀበለውን አደራ ለመወጣት የሚያደርገው ጉዞ ብዙ ነገር ያስተምረናል። ብዙዎቻችን በኦርቶዶክስ ኃይማኖት እያሉ አስማተኞች ስለሆኑ አንዳንድ ደብተራዎች ብናውቅም ለምን እንደዚህ ይሆናል ኦርቶዶክስ ክርስቶስን በሁለመናዋ እየሰበከች እንዴት እንዲህ ይሆናል ወዘተ እያልን የምናንሰላስለውን ጥያቄ ይመልሳል ብዬ አስባለሁ። ምስጢረ መርበብትን አስተምሮኛል፤ከሁሉም በላይ የኢትዮፕያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኅይማኖትን ጥልቅነትና የብዙ ረቂቅ ምስጢር ባለቤትነት ተምረበታለሁ።