ግሩም መጽሐፍ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ ልጅነታቸውንና አስተዳደጋቸውን የሚተርኩበት ክፍል ብዙ ትምህርት የሚሰጥ ነው፡፡ በ12 ዓመታቸው ትምህርት ጀምረው በ19 ዓመታቸው ኮሌጅ የገቡበት ከዚያም በኋላ ወደቤልጂየም ተጉዘው አዲስ ቋንቋ ተምረው ከባድ የሆነውን የህክምና ትምህርት በቀዶ ጥገና ስፔሻላይዝ እስከማድረግ የተማሩበት የመንፈስ ብርታት በጣም የሚደነቅ ነው፡፡ ከልክ ያለፈ ውፍረትን ለመቆጣጠር የሚያስችል በጨጓራ ላይ የሚገጠም መጠኑ የሚስተካከል ቀለበት ሆድ እቃ ሳይከፈት (በላፓራስኮፒክ መላ) የሚገጠምበትን ዘዴ በመፍጠር ለህክምናው ዘርፍ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ አዜብ ወርቁ በማይጎረብጥ አማርኛ ጥሩ አድርጋ ተርጉማዋለች፡፡