Jump to ratings and reviews
Rate this book

ከዕለታት … ግማሽ ቀን

Rate this book

287 pages, Paperback

First published September 1, 2020

8 people are currently reading
227 people want to read

About the author

አሌክስ አብርሃም

4 books59 followers

Ratings & Reviews

What do you think?
Rate this book

Friends & Following

Create a free account to discover what your friends think of this book!

Community Reviews

5 stars
48 (58%)
4 stars
21 (25%)
3 stars
7 (8%)
2 stars
6 (7%)
1 star
0 (0%)
Displaying 1 - 10 of 10 reviews
Profile Image for Estifanos.
153 reviews4 followers
March 14, 2024
የአሌክስ አብርሃምን ስራ ሳነብ ይህ የመጀመሪያዬ ነው።
አፃፃፉን በጣም ወድጄዋለሁ። በቀጣይም ሌሎች ፅሁፎቹን ለማንበብ ጓጉቻለሁ።
Profile Image for Jared Donis.
325 reviews58 followers
September 16, 2021
አሌክስ አብርሃም እጅግ በሚደንቅ ብቃት የሰራው ግሩም ስራ ነው። ምናልባትም ከዚህ በፊት ከጻፋቸው ድርሰቶች በላቀ መልኩ ይኸኛው ሳይጎላ እንደማይቀር አምናለሁ። ጥልቅ እይታዎች፣ በሳል ሐሳቦች እና ማራኪ ቋንቋ ታክሎበት የቀረበ ድርሳን ነው። አሌክስ በዚህኛው ድርሰቱ ግዜ ወስዶ፣ ራሱም በስሎ፣ ታሪኮቹንም በሚገባ ከሽኖ እንዳቀረባቸው ያስታውቃል። ደራሲ እንዲህ ራሱን በልጦ፣ ያለፉ ስራዎቹን ለዛ ሳይለቅ ላቅ ያለ ተወዳጅ ስራን ይዞ ሲቀርብ ማየት እጅግ ያረካል። በጣም ተደስቼ ያነበብኩት ስራ ነው። ድንቅ!

ከዚህ በተጨማሪ ሁለት ነገሮች አሌክስን እንዳመሰግነው ግድ ይሉኛል፦ አንደኛ፥ ባለፈው ዙቤይዳ በተሰኘው ድርሰቱ ቅር የተሰኘሁበትን ጉዳይ፥ ማለትም በገጸ ባሕሪያቱ እያስታከከ የሚሰብከውን ነገር በጣም ቀንሶ ታሪኮቹ እና ራሳቸው የገጸ ባሕሪያቱ ተፈጥሮ ለአንባቢው ተገቢውን መልዕክት እንዲያስተላልፉ መተዉ ነው። ሁሉም ስራዎች ውስጥ በሚያስብል ደረጃ የአሌክስ ስብከትና ድምጽ ሳይሆን እውነት የሚመስል የታሪክ ፍስሰት እና በሐቀኛ ብዕር የተሳሉ ሁነኛ (የምናውቃቸው የሚመስሉን) ሰዎች ናቸው የሚናገሩት። ሁለተኛ፥ የመጽሐፉ የህትመት ጥራት የሚያስመሰግነው ነው። አንዳንድ ደራሲያን እና አታሚ ድርጅቶች ወረቀትና ቀለም ለመቆጠብ ይሁን በሌላ ምክንያት ጥቅጥቅ ያሉ አንቀጾችን ለማንበብ የማይጋብዝ የወረቀት አይነት ላይ እንደ ነገሩ አሳትመው ይሸጣሉ። አሌክስ እና ማንኩሳ ማተሚያ ቤት እነዚህን ስስታምነቶች አስወግደው ለሕትመት ጥራት እንደተጨነቁም ያስታውቅባቸዋል። ሊመሰገኑ ይገባል።

ምናልባት አንድ ቅር ያለኝ ነገር ቢኖር ሁሉም ታሪኮች አተራረካቸው አቅጣጫ (point of view) ‘እኔ፣ እኔ…’ እያለ ስለሚሄድ ትንሽ እንደ መሰልቸት አድርጎኝ ነበር። ነገር ግን የእያንዳንዱ ታሪክ አዲስነት እና ሳቢነት ይህንን ድክመት ሞልቶታል ባይ ነኝ። ሙሉ ድርሳኑን በሁለት ቀን ውስጥ ነውና የጨረስኩት።

አሌክስ አሁንም በብዙ ሙሉ ቀኖች እና ታሪኮች ተባረክ!
1 review
February 14, 2021
Good
This entire review has been hidden because of spoilers.
Profile Image for Blen.
182 reviews6 followers
July 30, 2024
It's a shame it took me this long to get to this, it's been sitting on my shelves for a while. Such a great collection of short stories. It was so vivid and engaging it made me cry several times. New favorite Ethiopian author to look out for!
1 review
July 29, 2021
I Like it
This entire review has been hidden because of spoilers.
7 reviews
August 26, 2021
Its amazing book!it's lot of fun and also teaches you some lessons
Profile Image for Dereዘሲና.
2 reviews1 follower
April 24, 2022
አሌክስ አብርሃም በዶ/ር አሸብር እና ዙቤይዳ መፀሀፎቹ ባስደመመኝ የአጭር ታሪኮች የአፃፃፍ ስልት በከዕለታት ግማሽ ቀንም ተሳክቶለታል።
Displaying 1 - 10 of 10 reviews

Can't find what you're looking for?

Get help and learn more about the design.