Kidist G17 reviews9 followersFollowFollowReadApril 9, 2022ብዙ ቁጭት ብዙ ፀፀት ያለው መፅሃፍ ነው :: ትልልቅ አለመወለዶች አለመሆኖች ውስጥን ይፀፅታሉ :ቢሆን ኖሮዎች ቢሳኩ ቁጭቶች : አጭቆ የያዘ መፅሃፍ ነው ::ብዙ መንደዶች መብሸቆችን በመልካሙ የሚሰጥ ነው ::ምን ይሆን ነበር ??? ብዙ ጊዜ ስለዛ ትውልድ የተባሉትን በመስማት አለማንበብን አለማወቅን ጭፍን ግምት ብዙ ያሳጣል እንድል ያረገኝ ንባብ ነበር :: በመብሰል :በእድሜም በኑሮም እይታዎች ተለውጠው ተቀይረው የተበረከተ ስጦታ ነው:: ከድንፋታ የፀዳ እኔ ይሄንን አደረኩ ደሞ ያሁኑ ትውልድ ከሚል ማናናቅ እና መበሻሸቅ የራቀ ነው: ያሁኑንም የዛኛውንም ያስተዋለ ባዮግራፊ ነው:: ለሷም closure ያገኘችበት እንደሚሆን እገምታለው::አልፎ ማየትን ያህል መመልከቻ የለም ይህ ለታደለች ታድሏታል :ብርታቷንአደንቃለው :የደረሰባትን ፈተና :ያሳለፈችው ሁሉ በምሬት እጅ ያላሰጣት ነው :: እንዳለችውም ብዙ ልንማር ልንወያይ ልንግባባ ግድ ይለናል :::
Jared Donis339 reviews59 followersFollowFollowNovember 1, 2022ጥሩ መጽሐፍ ነው። ታደለች እንደ ሕይወት ተፈራ ሁሉ (ሊሻን አጎናፍርም አለች) የፍቅር ጓደኛዋን ታሪክ አስታውሳ ከነበረችበት ዘመን ጋር አዋድዳ አቅርባልናለች። ይህ አካሄድ በዚሁ ከቀጠለም ሁሉም ሴቶች ስለ ፍቅረኞቻቸው ጽፈው በማሳተም አዲስ ዘውግ ሊፈጥሩልን ሁሉ ይችላሉ። ወንዶች በዚህ መልኩ ስለ ፍቅር አጋሮቻቸው ጽፈው ማንበቤን አላስታውስም። ለምን ይሆን? ለማንኛውም 442 ገጾችን አንብቦ መጨረስ ቀላል ጉዳይ አልነበረም። ትኩረትን ሰቅዞ የሚይዝ ጉዳይ ብዙም ስላልነበረው ይሆናል። ሆኖም በጥሩ አጻጻፍ፣ በደንብ በተዋቀረ ቅርጽ ጥንቅቅ ብሎ የቀረበ ስለሆነ እና ሲነበብ ስለማያደነቃቅፍ ቀስ እያልኩም ቢሆን ጨርሼዋለሁ። እኔም በመጨረሻ ሁለት ነገሮች ብቻ ብዬ ልጨርስ። አንደኛ፣ ከሁሉም የመጽሐፉ ክፍል መውጫውን (የመጨረሻውን ክፍል ‘እንደ መውጫ’ ብላዋለች) ወደጄዋለሁ። እነዚህ ጥቂት ገጾች ዕምቅ የስነ-ጽሑፍ ችሎታዋን አሳይተውኛል። ለምን ሁሉንም የመጽሐፉን ይዘት በዚህ ዓይነት ለዛ እንዳልጻፈችው ግን ገርሞኛል። ምናልባት ብዙ ዝርዝሮችን ለማስታወስና ለማካተት ስትጨነቅ ቋንቋውን ትንሽ አሰልቺ አድርጋዋለች ብዬ አስባለሁ። ወደፊትም በትዝታ ሳትታሰር የምታሰበውን፣ ፍልስፍናዋን፣ ልምድዋን፣ ምክርዋን ብትጽፍልን አበረታታታለሁ። ሁለተኛው የገረመኝ ነገር ያንን ሁሉ ዝርዝር ማስታወሷ ነው። ምናልባትም አውሮፓ የሰለጠነች የታሪክ ተማሪ ስለበረች አብዛኛውን ነገር በሰነድ ማስታወሻ ይዛው ይሆናል፤ ቢሆንም ግን ከ40 አመታት በፊት የነበረን ጉዳይ ዘርዝራ የጻፈችበት መንገድ ‘እውነት ይህን ሁሉ አስታውሳው ነው ወይስ ፈጠራ አለበት?’ ብዬ እንዳስብ ፈትኖኛል።ከሞላ ጎደል ጥሩ ንባብ ነበር። ምስጋና ለጸሐፊዋ።