Martha H. Kidane46 reviews30 followersFollowFollowApril 27, 2021የመሀል ልጅ ራሳቸውን ችለው በቆሙ ግን ደግሞ ገጸባሕርያቱ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በተጋመዱ ታሪኮቹ መካከል የተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮቻችንን ይዳሳል። የባለታሪኮቹ ድምጽ ጠንካራ ነው። ስብእናቸውን ሲያጋቡብን እንደ ወራጅ ውሃ እያሳሳቁን ነው። ሀዘናቸው ጥልቅ፣ ፍቅራቸው ወሰን አልባ፣ የዋህነታቸው የሚያስቀና ገጸባሕርያትን እናገኛለን። ንጝር አልባ መሆንም ወሬም ያፈረሳቸውን የግንኙነት ካቦች በየታሪኮቹ መሀል እናገኛለን። የተለያዩ የእናትነትን ቀለማት፣ የአባትነትን ልኬቶችንም ከታሪክ ታሪክ እየተሻገርን እናያለን። ታዛዥ ልጅነትን እና አፈንጋጭነትንም እንደዚያው፤ ለደራሲዋ የመጀመሪያ መጽሐፍ እንደመሆኑ ሌሎች ታሪኮችን እንድታስነብበን እና በሌላ መጽሐፍ ድጋሚ እንድናገኛት ምኞቴ ነው።