Martha H. Kidane46 reviews30 followersFollowFollowMarch 18, 2022በሜሎሪና ያልተመለሱ የታሪክ ክፍሎች በዚህኛው መጽሐፍ መልስ የሰጠባቸው ይመስላል። እንደ መጀመሪያው መጽሐፍ ሁሉ ይህኛውም በታሪክ ፍሰቱ እንዲሁም ለቃላት የተደረገው ጥንቃቄ ታሪኩን በቀላሉ ለመከተል ያመቻል። የለመድናቸውን፣ የት ደርሰው ይሆን ያልናቸውን እና ደግሞ እንደ አዲስ የምንተዋወቃቸውን ባለታሪኮች አካቶ ከኢትዮጵያ ሱዳን ከሱዳን አሜሪካ እያጓጓዘ ጥበብን፣ ታሪክን እና የሰውን የልቦና ውቅር ሐዘን እና ደስታን የምንረዳበትን መንገድ በተጨማሪነትም የሕይወትን ዓላማ ወይም ጥሪ ማሳካትን ይዳስ ሳል። ደራሲው ታሪኩ አላለቀም እንዳሉንም የእኛም መገረም አላለቀም።