Jump to ratings and reviews
Rate this book

አለማወቅ

Rate this book
“ቤት በመቱ አሳቦች” ስንኞች ተቀንብቦና ታጥሮ የነበረው የደራሲው የእሳቤ ጓዳ ነፃ ወጥቶ “…መኖርም የሚጀምረው አለመኖርን ከመፍራት ነው” ብሎ የመጠየቅን ጉልበትና ፍልስፍና ያሳየን ደራሲ አሁን ደግሞ ሥጋና ደም ተላብሳ የተወለደች ህጻንን ከስድስት ሳምንት ዕደሜዋ በ“ዕሳቤ” አስጀምሮ ወደፊትና ወደኋላ በምልሰት እያናገረ የአእምሮን ጓዳ ያስበረብረናል። የ “መኖር መሠረት አለማወቅ ነው ይለናል በዚህኛው ቅጽ! ወላጅ እናትን ከመሃል አድርጎ የሁለት ትውልዶች የሕይወትን አተያይ፣ወግና ፍልስፍናም ያመላክተናል። በቁጥር አንድ አንደለመደው የሕክምና ሥነምግባር ያስተምራል። ሥውሩ የአእምሮ ጓዳ ለመበርበር ያለውን የሕክምና ዘዴና ጥቅም በተደራሲው ያስተዋውቃል፡፡የአዋቀው ዓለም አፍ ባልፈታች ጨቅላ ህጻን ዕይታ ምን እንደሚመስል የደራሲው አቀራረብ ያልተፈተሸና አስደማሚ ነው።አለመኖር ዘንድ አብረን ከርመን ተጠፋፍተንና ተነፋፍቀን የነበርን ገሃዳዋውና ምናባዋው ገጸባህርያት በ“አለማወቅ” ከህይወት ትምህርት ቤት ተመርቀው በጨቅላዋ፣በህጻንዋና ወጣቷ ሚጣ ዙርያ የህይወት ትዝብታቸውን በጤና፣በማህበራዊ ህይወትና በሥነአስተዳደር ዙርያ አሁንም ብዙ ይሉናል አብረንም አስከ መጽሃፉ መቋጫና ተዘያም በኋላ እንዘልቃለን።

ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ
(በአዲስ አበባ ዩኒቨርሰተ ኤመረተስ ፕሮፌሰር)

541 pages, Paperback

First published April 23, 2022

6 people are currently reading
47 people want to read

About the author

ዳዊት ወንድምአገኝ

3 books51 followers

Ratings & Reviews

What do you think?
Rate this book

Friends & Following

Create a free account to discover what your friends think of this book!

Community Reviews

5 stars
13 (81%)
4 stars
3 (18%)
3 stars
0 (0%)
2 stars
0 (0%)
1 star
0 (0%)
Displaying 1 - 2 of 2 reviews
Profile Image for Martha H. Kidane.
46 reviews30 followers
August 6, 2023
ስለዚህ መጽሐፍ ለማውራት ምናልባትም ተመልሼ ሁለት ሦስቴ ማንበብ ይኖርብኝ ይሆናል፤ አሁን ከምለው የተለዩ ሁለት እና ሦስት የተለዩ ሀሳቦችን ለማሰብ እንድችል። አለመኖር ላይ የተጀመረው የታሪክ ሰበዝ አለማወቅ ላይ የቀጠለ ቢመስልም ገጸባህርያቱ ስም አልባ ናቸው። ይህ ስም አልባነታቸው ግን ታሪካቸውን ለማወቅ ከመጓጓት፣ በሃሳባቸው እና በውስጥ የራስ ጋር ሙግታቸው ተሳታፊ ከመሆን፣ በሕመማቸው ተሳታፊ ከመሆን በአጠቃላይም በሕይወታቸው ተሳታፊ ከመሆን አያግደንም። በየገጹ ከራስ የሀሳብ ሙግት ጋር መላተምም ይኖራል። አጀማመሩ አልተስማማኝም ብላች ሁ ከንባብ ሳትገቱ እንድትጨርሱት አደራ እላች ኋለሁ። ከባድ የሞራል ጥያቄዎቻችሁን ከራሳችሁ ጋር ለመሞገት ተዘጋጁ።
Displaying 1 - 2 of 2 reviews

Can't find what you're looking for?

Get help and learn more about the design.