እጃችሁ በደም ተነክሩዋል….



እጃችሁ በደም ተነክሯል….…ወደ ኦሪታውያኑ ዘመን ልመልሳችሁ፤ ከዚያ ዘመን ውስጥ ፈርኦንን፣ ሙሴንና ኢያሱን እናንሣ፤ እነዚህን ሰዎች ደግሞ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ እንፈልጋቸው፤ የእነዚህ ቢጤዎች ናቸውና ዛሬ እንደጨቋኝ ገዢ ተቆጥረው የወቀሳ ናዳ የሚዘንብባቸው፤ የእነዚህ ቢጤዎች ናቸውና ዛሬ ከጭቆና ነፃ እንዳወጡን ተነግሮ የሰማዕት ሀውልት እንዲቆምላቸው የሚደረገው፤ የእነዚህ ቢጤዎች ናቸውና ዛሬ በህይወት ኖረው÷ ከወንድሞቻቸው የተቀበሉትን የትግል ዓርማ ከፍ አድርገው የተስፋይቱን ምድር እንዲጐበኙ የፍትህ አምላክ ስለ ፈቀደላቸው ደስ የምንሰኝባቸው!…‹ያ› የምንለው ትውልድ ተገልጦና ተነብቦ የማያልቅ መጽሐፍ እየሆነ ነው፤ ውለን ባደርን ቁጥር ተድበስብሰው የታለፉና ተቆፍረው የተቀበሩ ጉዶችና ገድሎችን እያደመጥን ነው፤ ያንን ትውልድ የሚያጀግኑ መዝሙሮች መስማት ብቻ ሳይሆን፤ የትውልዱን አካሄድ የሚነቅፉ ብዕረኞችም በየህትመት ሚዲያው ብቅ ብቅ እያሉ ነው፤ እነዚህ ብዕረኞች ትውልዱን ጀብደኛ ነበረ ነው የሚሉት፤ ከውጭ ሀገር የተኮረጀ ርዕዮት ይዞ ስለተነሣ ነው ተሰናክሎ የወደቀው ነው የሚሉት፤ ሕዝቡ የኔ ነው ብሎ የሚያምንበትን አምላኩን ከልቡ ለማስወጣት ይታገል ነበር ነው የሚሉት፤ ብዙ የሚሉት ነገር አላቸው፤ እንዲህ በማለታቸው አንዳንድ የያ ትውልድ አባላት ተቺዎቻቸውን ተቆጥተዋል፤ ሣታውቁን ነው የምትዘባርቁት ብለዋል፡፡          ጉዳዩ አጨቃጫቂ ነው፤ ክርክርና ንትርኩም የሚቀጥል! ያ ትውልድ ሜዳው ሰፊ ነው፤ በዚህ ሰፊ ሜዳ ላይ በ1960ዎቹና 70ዎቹ መጀመሪያ የነበሩ ወጣቶች ተጋጥመውበታል፤ ተጋጣሚዎቹ የማይከሰስና የማይወቀስ የሆነውን ንጉሳዊ አገዛዝን ገርስሰው ጥለዋል፤ የማይነካውን ከደፈሩ በኋላ ግን እርስ በርስ ተበላሉ፤ እርስ በርስ ተዋዋጡ፤ አብዮቱ ‹አፋጀሽኝ›ን ሆነ፤ መቧደናቸው ቀጠለ፤ ሞት፣ ስደት እና እስር የሁሉንም ቤት ለመጐብኘት ትጥቁን አጠበቀ፤ ደርግም፣ ኢሕአፓም፣ ሕወሓትም፣ መኢሶንም… ወዘተርፈው በሙሉ ልቡን ወያኔ አደረገ፤ ሸፈተ፤ ከተማውም ገጠሩም ዱሩም ገደሉም የእዚህ ትውልድ መሸሸጊያ ሆነ…
 •  0 comments  •  flag
Share on Twitter
Published on September 20, 2013 09:21
No comments have been added yet.


እንዳለጌታ ከበደ's Blog

እንዳለጌታ ከበደ
እንዳለጌታ ከበደ isn't a Goodreads Author (yet), but they do have a blog, so here are some recent posts imported from their feed.
Follow እንዳለጌታ ከበደ's blog with rss.