ብቻነት



ብቻነት ልቤ ውስጥ ክረምት ገባ የሀዘን ውሽንፍርየብቻነት ዶፍገላዬን አራሰው      ወየው!ልቤን!ልቤን!!ልቤን!!!ነፍሴ ጎርፍ አትወድምነፍሴ ውርጭ አትለምድምጭጋግ ይጨንቀኛልብርሃን ይርበኛል…ሰው የማታ ራቴሰው የምኞት ጓዜማን ይሆን ሳምራዊማን ይሆን ቅን ወዳድእኔ ነኝ ባይ ማነውየእግዜር አምባሳደርፀሃይን ሰርቆልኝጨረቃዋን ጭምርበልቡ ሙዳይ ውስጥልቤን የሚያሳድር፡፡

 •  0 comments  •  flag
Share on Twitter
Published on August 24, 2013 07:04
No comments have been added yet.


እንዳለጌታ ከበደ's Blog

እንዳለጌታ ከበደ
እንዳለጌታ ከበደ isn't a Goodreads Author (yet), but they do have a blog, so here are some recent posts imported from their feed.
Follow እንዳለጌታ ከበደ's blog with rss.